Create New Playlist

Add a cover pic of your own choice

(Optional)

Name

AI Cover Generator

4 credits

Not enough credits (0/4).

Logout

Are you sure you want to Logout?

Close

ስራ ፈተህ እንጂ (If Only You Tried) 1 by Dad

SongGPT
ስራ ፈተህ እንጂ (If Only You Tried) 1 by Dad - Ethiopian Soul music cover art

ስራ ፈተህ እንጂ (If Only You Tried) 1

Ethiopian Soul

0:002:55
Lyrics
Description
[Verse 1]
ስራ ፈተህ እንጂ ሚሰራ መች ጠፋ
ተከምሮ ሳለ ሁሉም በወረፋ
እንዴት ትለኛለህ ለኔ ስራ ጠፋ
ስንፍናህ አይሎ አጀዝቦህ ሳለ
ትኩረት አንተን ሸሽቶ ከውጪ ከዋለ
ግዜህን በአግባቡ አበካክነከዉ
ያላንዳች ቁምነገር አጠፈፋተከዉ
[Pre-Chorus]
የሰራው ሲቀየው ፍሬው ሲያፈራለት
እሱ ሲንቀሳቀስ ተቀምጠህ ከቤት
ትችት እና ዝልፊያ ቁም ነገር መስሎህ
እሱን ስትተርብ ቁጭ ብለህ ትውላለህ
[Chorus]
እነዛ ደነዞች ያንተ ብጤ ገልቱ
ጎደኛ ተብዬ አብረውህ ሲደሰቱ
ተሳቀልኝ ብለህ ስትቀባጥር ውለህ
አንዳች ግፍ ሳትፈራ ሁሉንም ቀባጥረህ
[Verse 2]
"እሱ ሰርቆ ነው እሱ ደሞ ወርሶ
ጅቦችን ጋልቦ ነው ለጠንቋይ አጉርሶ
አሷስ ባልጋ እኮ ነው ነውር ስራ ሰርታ
ወንድ ነው የገዛላት በአንድ ቀን በማታ"
እያልክ እነደፃድቅ ነውር እንደሌለው
ሁልግዜ ንፁ ግድፈት እንደማያውቀው
ስትተች ስታጣጥል ጣትህን ስትቀስር
ላንተ ሳይታይህ ያለብህ ችግር
[Pre-Chorus]
በነሱ መቀየር አንተ ስትፎክር
ውለህ ስትግማማ ሁሉን ስትቀባጥር
ልክ መሸት ሸት ሲል ለብቻህን ስትሆን
ትታዘበዋለህ እራስህ ስታጤን
[Chorus]
እነዛ ደነዞች ያንተ ብጤ ገልቱ
ጎደኛ ተብዬ አብረውህ ሲደሰቱ
ተሳቀልኝ ብለህ ስትቀባጥር ውለህ
አንዳች ግፍ ሳትፈራ ሁሉንም ቀባጥረህ
[Bridge]
ምንም ምላስ ብቻ አንዳች እንደሌለህ
ከማማረር በቀር ምስጋና እንደሌለህ
እራስህን በጅጉ በጣም ትጠላለህ
መሄጃም የለህም ራስህ ታጠፋለህ
[Chorus]
እነዛ ደነዞች ያንተ ብጤ ገልቱ
ጎደኛ ተብዬ አብረውህ ሲደሰቱ
ተሳቀልኝ ብለህ ስትቀባጥር ውለህ
አንዳች ግፍ ሳትፈራ ሁሉንም ቀባጥረህ
[Outro]
ራስህ ታጠፋለህ
ራስህ ታጠፋለህ
መሄጃም የለህም
ራስህ ታጠፋለህ